SUPPORT THE E D P

A party of the future

ቪ ኦ ኤ እና አቶ ልደቱ

የአቶ ልደቱ ስም በሆነ ጉዳይ ሲንሳ እንደ ጉንዳን ሁል ጊዜ ስብስብ ብለው ምናምን የሚጽፉ ትንንሽ ነፍሳት አስተውያለሁ። ብዙዎቻቸው ከሁለት ሶስተ መስመር አሉባልታ ውጭ ቁምነገር አይጽፉም። እንዳንዴ ብዙ መስለው ለመታየትም የሚፈልጉ ይመስላሉ። ግን እዚህ ክፍል ብቅ ብለው ትፈታቸውን የመረጉትንና ሌላም ክፍል የታዩትን ደምሬ ደማምሬያቸው ስቆጥራቸው የሁለት እጅዎች ጣቶች አያህሉም።  የልደቱ ስም ሲነሳ ክህደቱ፣ ባንደ፣ ወያኔ እንዲሉ የተሰጣቸው ስራ ያለ ይመስላል።

የአቶ ልደቱ ጠላቶች ልደቱን በድንብ ያውቁታል። አቶ ልደቱ ንጽሁ፣ እውነተኛ፣ ለማንም የማያጎበድድ ደፋር ሰው መሆኑን አሳምረው ያውቃሉ። አቶ ልደቱን በቀላሉ ከፖለቲካው መድርክ ማስወጣት እንደማይችሉ ሰለሚያውቁ በኢትዮጵያ ታሪክ ተወዳዳሪ ያልተገኝለትን የተቀናበረ ከፍተኛ የአሉባልታ ዘመቻ አካሄዱ። በቁጥር ሰማኒያ የደረሱ የሀሰት ወሬዎች ተፈበረኩ። የግል ጋዜጦች፣ በራሪ ወረቀቶች፣ ኢንተርነት ድረ ገጾች፣ ፓልቶክ ከፍሎች ሁሉ የአቶ ልደቱን ስም ማጉደፍ ላይ ተረባረቡ። ቪኦኤ ውስጥ ያሉ ግልብ ጋዜተኞችም የድረሻቸውን አደረጉ። እነአዲሱ አበበነ ትዝታ በላቸው የተቻላቸውን ያህል አራገቡ። ብዙ ሰውም በወቅቱ አመናቸው።

ቀደምት፣
 "በአቶ  ልደቱ  ላይ  ለደረሰው  ከፍተኛ  የስም  ማጥፋት  ዘመቻ  ቪኦኤ  ከፍተኛ  ድርሻ  እንዳለው  በታሪክ  ተመዝግቦ  የሚኖር  ሃቅ  ነው።  በዚህ  ውስጥም  የተወሰኑ  ሰወች  ልዩ  ሚና  አላቸው። እነዚህ  የቪኦኤ  ሰዎች  በዚህ  ምግባራቸው  ግባቸው  ምን  እንደሆነ  በጣም  ግራ  የሚያጋባ  ሆኖ  ስለቆየ  አሁን  አቶ  ልደቱ  በ  ወ /ሮ  ትዝታ  ላይ  ያቀረቡት  ቅሬታ  ተገቢነት  ያለው  ነው።" ሲልልጽፎአል።

 ትክክል ነው።"

ከዚህ ሁሉ ርብርብ በሁዋላ አሉባልትኛቱ ተበታተኑ፣ ፈራረሱ። የፍርሻው ሂደት አሁን ደረስ አላቆመም።  እርስ በርስ መወነጃጀሉም እንደቀጠለ ነው። አቶ ልደቱና ፓርቲው ግን እነሱ እንዳስቡት እልሞቱም። በርግት አሉባልታው የተቀናበረ  ስለነበር ፓርቲውና አመረሩ ላይ ጉዳት ደርሶአል። በርካታ  የፓርቲው ደጋፊዎች ልደቱ፣ የወያኔ ሰላይ ነው፣ ሽራቶን ነው የሚያድረው፣ የሚሎዮን ብር መኪና ነው የሚነዳው የሚለውን ርካሽ ወሬ ባያምኑም፣ የቅንጅት መሪዎች ቃሊቲ ሲገቡ ልደቱ የፓርላማውን መድረክ ለመታገያ ለምን እንደመረጠ ባለመረዳት አኩርፈው ቀርተዋል።

ጊዜ ግን የራሱን ታሪክ ይጽፋል። ደፋርም የውሸትን ጉም በትኖ ይወጣል። አሁን የምናየው ያ ነው። የልደቱን ዳግማይ ልደት። ያ ደግሞ በተራው ጠላቶቹን ያስደነግጣቸዋል። እናም እንደገና በስም ማጥፋትና አሉባልታ መንዛት ተግባር ይሰማራሉ።  ህዝብን ሁሌ ማታለል ይቻል ይመስላቸዋል።

የግዛቸውን ጡፍ እንይ።
"አይ ልደቱ !!! Poor Lidetu,
በጣም የምትገርም ሰው ነህ :: ብለህ ብለህ ደግሞ ይህን መጠየቅ አልነበረብኝም :: ይህኛውን ግን መጠየቅ ነበረብኝ ትል ጀመረህ ??

ገና ካሁን ስልጣን ሳትይዝ በጋዚጠኞች ላይ ማግረምረም ከጀመርህ ስልጣም ይዘህ ቢሆንማ ከመለስ የባስህ ጸረ -ጋዚጠኛ እንደምትሆን በመጠኑም ቢሆን ይህ አመላካች ነው ::

ትዝታ ደግ አደረገች :: በማለት ጡፍ የሚጀምር ሰው ብስለቱ ያጠራጥራል። እንዲህ አይነት አባባል የልጆች አባባል ነው። ሴትነትም ይነበብበታል። ግዛቸው ትንሽ ልጅ ሊሆን ይችላል። እናቱ ስታወራ  በሰማው ተመርቶ ሊሆን ይችላል አቶ ልደቱን  የጠላው እና አይፈረድበትም። እናትየውም አይፈረድባትም በቪኦኤ የሰማቸው የአዲሱንና የትዝታን ቅጥፈት አምና ሊሆን ይችላል። ያም ሆን ይህ የግዛቸው ጮርቃ ጭንቅላት ውስጥ የተወታተፈ የወሬ ቡትቶ እንዳለ ያስታውቃል። ያን ቡትቶ አውጥቶ እውነትና እውቀት ባንዴ ማስገባት ቀላል አይሆንም መጀመር ግን አይከፈም።

ግዛቸው፣
መጠየቅ የሚፈልገውን ጥያቄ መምረጥ የሚችለው ጋዚጠኛው እራሱ ነው እንጅ ተጠያቂው ነው እንዴ ?
 ብለህ ጠይቀሃል።
አዎ፣ ጋዜጠኛው በአሉባልታ ላይ የተመሰረቱ፣ በጣም የሰለቹ ጥያቄዎችን በማቅረብ የተጠያቂውንና ያድማጩን ጊዜ ሲያቃጥል ዝም ማለት አልተቻለም። ልደቱ እኮ ነው፣ ሰውየው። እነኩዋን ቪኦኤ  ለምን ሲ ኤንኤን እይሆንም። የሚፈራ ይመስልሀል። ይሄ ኮ ነው፣ ከቅንጅቶች ጋር ያቃቃረው። ልድቱጋ ይሉኝታ  የለም። ሽማገሌ ነው፣ ዶክተር ነው፣ ሚንስተር ነው፣ ምቄስ ናቸው ገለመሌ  የለም፣  ካልመሰለው እዛው ነው የሚነግርህ።  ለመሆኑ እነ ፕሮፌስር መስፍን በለው ፕሮፌስር በየነ፣ ጉዲና በለው ሀይሉ ሻውል  ልደቱ  ፊት እንደሚቀዝኑ ታውቃለህ? ልደቱ  ፊት መጨመላለቅ እንደሌለ ታውቃለህ? ማናባቱ  ነው ልደቱ  እያለ ከህገ ማህበሩ ውጭ ዝንፍ የሚል። ማን ነው ከአጀንዳ ውጭ የሚሙለቸለጭ። ልደቱ ለአምባገነኖች አይመችም። ልደቱ ሳይሰሩ ለሚኮፈሱ አይጥምም። ልደቱ ድግሪ ተሸክመው ለሚያውደለድሉ አይስማመም። ስለዚህ አይፈለግም።

ግዘቸው፣ እንደ ልደቱ አይነት ሰው አይወደድም።  እንደማህበረሰብ እኛም እንዲህ አይነት ሰው በመሃላችን ለማስተናገድ መብቃታችንን እጠራጠራለሁ። ለምሳሌ ምንይባላል የጻፈውን እንመልከት።

ምንይባላል
ይህ ልደቱ የሚባል ስው በጣም ይገርማል :: ባለፈው ትግስቱን ሰጥቶኝ ኢቲቪን ሰመለከት የኢትዮጵያን ህዝብ 'የተማረንና በዕድሚ የገፋ ሰው አምላኪ ' እያለ ሲሳደብ ስማሁት : እጂግ የወረደ አስተሳሰብ !! የሚገርመዉ ይህን ብሎ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ደበተር ይዞ አየሁት :: እስኪ አሁን ህዝቡ በተምህርት እና በእድምየ ልምድ ያካበቱትን ይከተል ወይስ እንደሱ አይነቱን ፍንዳታና ያልተማረ ይከተል ?


በመጀመሪያ ልደቱ የኢትዮጵያን ህዝብ 'የተማረንና በዕድሚ የገፋ ሰው አምላኪ ' ብሎአል ወይ የሚለው ጥያቄ አለ። "ምን ይባለል" ሰማሁ ብሎ ነው ያቀረበልን። የምንሰማውን ነገር ሁሉ ቃል በቃል ማስቀመጥ ቀላል አይደለም። የምናስቀምተው የገባንን ነው። ማለትም ምንይባላል የጻፈው ልደቱ ሲናገር እሱ የገበውን እንጂ ቃል በቃል ልደቱ  ያለውን አይመስለኝም።
ለምሳሌ ፣ እኛ የተማረና በእድሜ  የገፋ ሰው እናመልካለን ብሎ ሊሆን ይችላል።
ወይም ብዙ  ሰው የተማረና በእድሜ  የገፋ ሰው ያመልካል ብሎ ሊሆን ይችላል። ይህ አባባል በነምንይባለል ጭንቅላት ውስጥ ካለው ጭፍን ጥላቻ ጋር ሲለወስ፣ የኢትዮጵያን ህዝብ 'የተማረንና በዕድሚ የገፋ ሰው አምላኪ ' እያለ ሲሳደብ ስማሁት ያሰኛል።

እስኪ አቶ ለደቱ አለ የተባለውን ራሱን እንውሰድ፣ በምን ርእስ ስር ነው እንዲህ ያለው? አውደ ውይይቱ (context)ምን ነበር? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። ይህን ማወቅ በጣም ወሳኝነት አለው። አደማመጡ፣ ቃናው(tonality) ራሱ ትርጉም ይቀይራል። ቃላት ሲጻፉና  ሲደመጡ የሚሰጡት ትርጉም ይለያያል።  ከረጅም ቃለ ምልልስ ውስጥ አንድ መስመር ቁንጥር አደርገን እገሌ እንዲ አለ ማለት ከአሉባልታ ተለይቶ አይታይም። በተረፈ  ግን ከአቶ ልደቱ አባበል መረዳት የምችለው፣ በኢትዮጵያ ለደረሰው ችግር ዋና ተጠያቂው ምሁሩ ነው የሚል እንደምታ ያለው ይመስለኛል። አቶ ልደቱ እዚህ ድምዳሜ ላይ ያለ ምክንያት አልደረሰም።

በኢትዮጵያ የመደብ ጭቆና፣ የብሄር ጭቆና፣ የጾታ ጭቆና  ወዘተርፈ እያሉ የተለያዩ አፍራሽ ንቅናቄዎችን የቀሰቀሱ፣ ያነሳሱና የመሩት እንያ ተጨቁነዋል የተባሉት ወገኖች ራሳቸው ሳይሆኑ እነሱን እንወክላለን የሚሉት ምሁራን ናቸው። ከዚህ በመነሳት ይመስለኘል አቶ ልደቱ ያን የለው፣ ይህን ሀሳብ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ብዙ ሰው ይጋራዋል ብዬ አምናለሁ።

በርግጥ አቶ ልደቱ ካልመሰለው ህዝብን ሳይሆን ብዙ ሰዎችን፣ ቡድኖችን፣ ማህበራትን፣ ድርጅቶችን፣ መንግስትን በድፍረት የሚነቅፍበት ግዜ አለ። ህዝብን ለመደለል ህዝቡ  ነቅቶአል፣፣ በቅቶአል፣ መንትቆአል እንደሚሉት አይልም። እንዲያውም ደፍሮ ህዝባችን ገና ነው፣ ሲል የሰመሁት አንድ መሪ ቢኖር ልደቱ ነው። ያ ባህሪውን የምንወድለት እንዳለን ሁሉ፣ የሚጠሉትም አሉ። በሱ በኩል ግን ማን ወደደው ማን ጠላው ጉዳዩ አይመስለኝም። ጉዳዩ ከሂልናውና ከአገር ዘለቂ ጥቅም ጋር ነው። እንደ ጋዜጠኛ ስለመውደድና መጠላት የሚጨነቅ የፖለቲካ መሪ ዋጋ የለውም።

open letter to VOA

Welcome